Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 1:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነርሱም ቀደም ሲል ሎዛ ትባል ወደነበረችው ወደ ቤቴል ሰላዮችን በላኩ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የዮሴፍም ወገን ቀደም ሲል ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ወደ ቤቴል ከተማ ሰላዮችን በላኩ ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የዮሴፍ ልጆች ቤቴልን የሚሰልሉ ሰዎች ላኩ፤ የከተማይቱ ስም አስቀድሞ ሎዛ ይባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እነ​ር​ሱም ሰፍ​ረው ቤቴ​ልን ሰለ​ሉ​አት። አስ​ቀ​ድ​ሞም የዚ​ያች ከተማ ስም ሎዛ ይባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የዮሴፍም ወገን ቤቴልን የሚሰልሉ ላኩ። አስቀድሞም የከተማይቱ ስም ሎዛ ይባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 1:23
10 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፥ አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።


ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ፥ ባረከኝም


ያዕቆብም፥ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሎዛ መጡ፥ እርሷም ቤቴል ናት።


ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ አምስት ኃያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፥ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው። መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ።


ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ላከ፤ እንዲህም አላቸው፦ “ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ፤” ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።


የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።


ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል በሎዛ አቅጣጫ ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ወገን አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።


የዮሴፍ ወገን ደግሞ ቤቴልን ሊወጉ ወጡ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ነበር።


የዮሴፍም ልጆች ዕጣ በኢያሪኮ ወንዝ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳው አድርጎ ከኢያሪኮ በተራራማው አገር በኩል ወደ ቤቴል ወጣ፤


ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ግዛት በኩል ወደ ዓጣሮት አለፈ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios