Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በሩ በሚዘጋበት ጊዜ ሲመሻሽ ሰዎቹ ወጥተው ሄደዋል፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ትደርሱባቸዋላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጨልሞ የቅጥሩ በር ከመዘጋቱ በፊት ወጥተው ሄደዋል፤ በየት በኩል እንደ ሄዱ ግን እኔ አላውቅም፤ ልትደርሱባቸው ትችላላችሁና ፈጥናችሁ ተከታተሏቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጊዜው መሽቶ በመጨለሙ በሩ ሲዘጋ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ ብታሳድዱአቸው ትደርሱባቸዋላችሁ” አለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በሩም ሲዘጋ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፥ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፥ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ታገኙአቸውማላችሁ አለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 2:5
11 Referencias Cruzadas  

በዚያም ሌሊት ስለ ሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፤


በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉ አይረግፍም ፍሬውም አያልቅም፤ ውኃው ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኩር ያፈራል፤ ፍሬው ለመብል ቅጠሉም ለፈውስ ይሆናል።


እንደትሩፍ የተውኳቸውን እነዚያን ይቅር እላቸዋለሁና በዚያን ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ነገር ግን በዚያ ምንም አይገኝም።


በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጽግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ለማምጣት ሌሊትና ቀን አይዘጉም።


ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።


ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ።


ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርሷም እንዲህ አለች፦ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም፤


እርሷ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፤ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር።


ሳኦል ዳዊትን እንዲይዙት ሰዎች በላከ ጊዜ ሜልኮል፥ “እርሱ ታሟል” አለቻቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios