Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 6:69 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

69 እኛስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም፤” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

69 አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደ ሆንህ አምነናል፤ ዐውቀናልም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

69 እኛስ አምነናል፤ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አንተ እንደ ሆንክም ዐውቀናል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

69 እኛስ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ አንተ እንደ ሆንህ አም​ነ​ናል፤ አው​ቀ​ና​ልም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

69 እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:69
18 Referencias Cruzadas  

እርሷም “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ” አለችው።


እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ “የእግዚአብሔር መሢሕ ነህ፤” አለ።


ቀጥሎም፥ “እናንተሳ ማን ትሉኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፤ “አንተ ክርስቶስ ነህ” አለው።


ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


ወንጌሉም ስለ ልጁ፥ በሥጋ ከዳዊት ዘር እንደመጣ፥


ነገር ግን ኢየሱስ መሢሕ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።


ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።


እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሢሕን አግኝተናል” አለው፤ ትርጓሜውም “ክርስቶስ” ማለት ነው።


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።


“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከኛ ምን ትሻለህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደሆንህ ዐውቃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!”


ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።


በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውሃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ ውሃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?” አለው።


የእግዚአብሔር ልጅ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፥


የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን እናንተ ‘ትሳደባለህ፤’ ትሉታላችሁን?


ይህም ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ፍጽምናው እስክንደርስ ድረስ ነው።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነናልም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፥ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios