Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሌሎቹም ደቀመዛሙርቱ “ጌታን አይተነዋል፤” አሉት። እርሱ ግን “የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ላይ ካላየሁ፥ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ውስጥ ካላስገባሁ፥ እጄንም በጎኑ ቊስል ውስጥ ካላስገባሁ አላምንም፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፣ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። እርሱ ግን፣ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፣ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ስለዚህ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ቶማስን “ጌታን አየነው” አሉት። እርሱ ግን “በምስማር የተወጉትን እጆቹን ካላየሁና ጣቴን በምስማር በተወጋው ውስጥ ካላገባሁ፥ እጄንም በጐኑ ቊስል ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም፥ “ጌታ​ች​ንን አየ​ነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የች​ን​ካ​ሩን ምል​ክት በእጁ ካላ​የሁ፥ ጣቴ​ንም ወደ ተቸ​ነ​ከ​ረ​በት ካል​ጨ​መ​ርሁ፥ እጄ​ንም ወደ ጎኑ ካላ​ገ​ባሁ አላ​ም​ንም” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ፦ “ጌታን አይተነዋል” አሉት። እርሱ ግን፦ “የችንካሩን ምልክት በእዶቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:25
25 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ዓይነት ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?


እነርሱ ግን አላመኗትም።


ካልታዘዙትም በስተቀር፥ ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?


ወንድሞች ሆይ! ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤


ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀመዝሙር ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ዘለለ።


እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሢሕን አግኝተናል” አለው፤ ትርጓሜውም “ክርስቶስ” ማለት ነው።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉ፤ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤


“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ነው፤ አሁን ከመስቀል ይውረድና እኛም በእርሱ እናምናለን።


ከዚህም ሁሉ ጋር እንደገና በደሉ፥ ተኣምራቱንም አላመኑም፥


ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን ሰማ ብዬ አላምንም ነበር።


ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወረድኸኝ።


እነርሱም ተመልሰው ይህንኑ ለቀሩት ነገሯቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱንም አላመኗቸውም።


ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማዕድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፥ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ።


ከዚያም በኋላ ቶማስን “ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ ውስጥ አስገባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን፤” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios