Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 18:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ጲላጦስም እንደገና ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ጲላጦስም ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን አስጠራና፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ጲላጦስ እንደገና ወደ ግቢው ተመልሶ ገባ፤ ኢየሱስንም ጠርቶ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ጲላጦስም እንደ ገና ወገ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ፦ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 18:33
25 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፤ ነገር ግን አይሁድ “ይህን ሰው ከፈታኸው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ።


እየቀረቡም “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር።


ጲላጦስም “እንግዲያውስ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ፤ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው።


የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዞ ሊቀበለው ወጣና “ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፤” እያሉ ጮኸ።


ጲላጦስም፥ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢየሱስም፥ “አንተው አልኸው፥” በማለት መለሰለት።


ኢየሱስ በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም “አንተ አልህ” አለው።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


ተመልሶም ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን “አንተ ከየት ነህ?” አለው። ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።


“አንቺ የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል፤” ተብሎ እንደ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።


ናትናኤልም መልሶ “መምህር ሆይ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” አለው።


ጌታ ቅጣትሽን አስወግዷል፥ ጠላትሽንም አጥፍቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ጌታ በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አትፈሪም።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ ሰበሰቡ።


“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።


ኢየሱስም መልሶ “አንተ ይህን የምትለው ከራስህ ነውን? ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነገሩህ?” አለው።


ጲላጦስ “እውነት ምንድነው?” አለው። ይህንንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጣና “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትም።


ጲላጦስም በድጋሚ ወደ ውጭ ወጥቶ “እነሆ፥ አንዲት በደል እንኳን እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios