Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 16:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤”፥ ደግሞ “ወደ አብ እሄዳለሁና፤ የሚለን ነገር ምንድነው?” ተባባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ፣ “  ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም፣ ‘ወደ አብ ስለምሄድ’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶች፥ “ይህ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ ወደ አብ እሄዳለሁ’ የሚለን ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው፦ “ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ፦ “ወደ አብ እሄዳለሁና” የሚለን ይህ ምንድር ነው?” ተባባሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 16:17
12 Referencias Cruzadas  

“ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።”


“አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ከእናንተም ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።


እነርሱ ግን የሚላቸው አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤’ ስላልሁ፥ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?


ቶማስም “ጌታ ሆይ! ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን ነገር በመጀመሪያ አላስተዋሉም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከከበረ በኋላ በዚያን ጊዜ ይህ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይህንም እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው።


እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፤ ይህም ንግግር ተሰውሮባቸው ነበር፤ የተናገረውንም አላወቁም።


እነርሱም የተናገራቸውን ቃል በልባቸው አሳደሩት፤ ነገር ግን፥ “ከሙታን መነሣት” ምን ማለት እንደሆነ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።


“እንዳትሰናከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ።


የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላኛው ይሁዳ “ጌታ ሆይ! ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው።


እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፤ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህም ነገር እርሱን ለመጠየቅ ፈሩ።


“እንግዲህ ‘ጥቂት’ ሲል ምን ማለቱ ነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios