Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 11:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ኢየሱስም በድጋሚ በጥልቅ ኀዘን ተውጦ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ተነክቶ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም በድንጋይ የተገጠመ ዋሻ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ በጣም እያዘነ ወደ መቃብሩ ሄደ፤ መቃብሩ በድንጋይ የተዘጋ ዋሻ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እርሱም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 11:38
12 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ፥ በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው፥ ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ።


መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ?


አንተም የሰው ልጅ ሆይ አልቅስ፥ ወገብህን በማጉበጥና በምሬት በፊታቸው አልቅስ።


ጌታም እንዲህ አለው፦ በከተማይቱ መካከል፥ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኩሰት ሁሉ በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ።


ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብሩ አኖረው፤ በመቃብሩ በር ላይ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።


ሄደውም መቃብሩን ድንጋዩን በማተም ጠባቂዎች አቆሙ።


ዮሴፍም በፍታ ገዛ፤ ሥጋውንም አውርዶ በበፍታው ከከፈነው በኋላ፥ ከዐለት በተወቀረ መቃብር አኖረው፤ የመቃብሩንም ደጃፍ በድንጋይ ገጠመው።


እርሱም በመንፈሱ እጅግ በመቃተት፥ “ይህ ትውልድ ምልክት የሚፈልገው ለምንድን ነው? እውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም” አለ።


ድንጋዩንም ከመቃብሩ ወዲያ ተንከባሎ አገኙት፤


ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ ከእርሷም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤


ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለሞ ሳለ በማለዳ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos