Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 10:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን እናንተ ‘ትሳደባለህ፤’ ትሉታላችሁን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ታዲያ፣ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ለራሱ ለይቶ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን፣ ‘ተሳድበሃል’ ብላችሁ ለምን ትወነጅሉኛላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ታዲያ፥ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስለ አለ ስለምን ‘በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ትናገራለህ’ ትሉታላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነኝ ብላ​ችሁ፥ አብ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ወደ ዓለ​ምም የላ​ከ​ውን እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ? ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የተቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 10:36
39 Referencias Cruzadas  

ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።


“በማሕፀን ውስጥ ሳልሠራህ በፊት አውቄሃለሁ፥ ከማሕፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌ ሾሜሃለሁ።”


ነገር ግን ኢየሱስ መሢሕ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ከእነርሱም ዘር ክርስቶስ በሥጋ መጣ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድስና መንፈስ ከሙታን በመነሣት በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ መገለጡ ነው፤


ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።


አይሁድም መልሰው “እኛ ሕግ አለን፤ በሕጋችን መሠረት ሊሞት ይገባዋል፤ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ አድርጎአልና” አሉት።


ይህም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም፥ አባት ሆይ! በእኔ እንዳለህና እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም እንዲያምን ነው።


ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ ሁሉ እኔም ወደ ዓለም ላክኋቸው፤


የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፤ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፤ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።


እኛስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም፤” ብሎ መለሰለት።


ሕያው አብ እንደ ላከኝ፥ እኔም በአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚመገበኝ ደግሞ በእኔ ሕያው ይሆናል።


ፈቃዴን ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።


“እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ፤ ፍርዴም ቅን ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።


እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።


በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሏልና የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው።”


የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በጌታና በመሢሑ ላይ ተማከሩ፦


የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤


ሕግ ከሥጋ ድካም የተነሣ ማድረግ ያልቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌና ስለ ኃጢአት ልኮ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ፤


ኢየሱስም አላቸው “እግዚአብሔርስ አባታችሁ ቢሆን ኖሮ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።


የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።


እነሆ፥ ለአሕዛብ ምስክር፥ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።


የተቀጠቀጠን ሸንበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።


እነሆ ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።


መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios