Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 10:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ነገርኋችሁ፤ ነገር ግን አታምኑም፤ እኔ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች ስለ እኔ ይመሰክራሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ታምራትም ስለ እኔ ይናገራሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የምሠራው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አታ​ም​ኑ​ኝም እንጂ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እኔ በአ​ባቴ ስም የም​ሠ​ራው ሥራ እርሱ ምስ​ክሬ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ “ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 10:25
17 Referencias Cruzadas  

የምሠራ ከሆነ ግን፥ እኔን እንኳን ባታምኑ፥ አብ በእኔ እንደሆነ እኔም በአብ እንደሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።”


ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ፤” አላቸው።


እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ይህም ካልሆነ ስለ ሥራዎቹ ስትሉ እመኑኝ።


እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌላ ብዙ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤


ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግም፤ እነርሱ ግን በእርሱ አላመኑም።


የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፥ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን ያደርጋልና።


ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።


እንግዲህ “በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እርሱ እንደሆንሁ ካላመናችሁ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁና፤” አላቸው።


ደግሞም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።


ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበትና፥ “ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ሰው ካደረጋቸው ምልክቶች የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።


እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ “መምህር ሆይ! ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል ማንም የለምና፤” አለው።


“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁት፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤


አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ለማየት በመመኘት ሐሤት አደረገ፤ አየም፤ ደስም አለው።”


እኔ የአባቴን ሥራ የማልሠራ ከሆነ አትመኑኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios