Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 35:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤ መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ክፋ​ትህ ይጎ​ዳ​ዋል፤ ለሰ​ውም ልጅ ጽድ​ቅህ ይጠ​ቅ​መ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 35:8
15 Referencias Cruzadas  

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ ለበረከትም ትሆናለህ፤


እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።


ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?


ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፥ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጣራሉ።


አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”


እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ።


ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፥


ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፥ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።


ቅጥሩን የሚሠራ፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አላገኘሁም።


እርሱም፦ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደመጣባችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።


ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል፤” አለኝ።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ስላልታመነ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በበደሉ ብቻውን አልሞተም።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos