Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ አሁንም ስሜ በተጠራበት ቦታ፣ በታመናችሁበት ቤተ መቅደስ፣ ለአባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁት በዚህ ስፍራ እንዲሁ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ በሴሎ ያደረግኹትን በዚህ በምትታመኑበት በቤተ መቅደሴ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁት በዚህ ቦታ በሴሎ ያደረግኹትን ደግሜ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚህ በሴሎ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት፥ እና​ን​ተም በም​ት​ተ​ማ​መ​ኑ​በት ቤት ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋ​ችሁ ስፍራ እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 7:14
28 Referencias Cruzadas  

‘የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ፥ የጌታ መቅደስ ይህ ነው’ እያላችሁ በእነዚህ የሐሰት ቃላት አትታመኑ።


መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፦ እነዚህን አስጸያፊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለማድረግ ‘እኛ ድነናል’ አላችሁ።


የሴሎምን ማደሪያ ተዋት በሰዎች መካከል ያደረባትን ድንኳኑን፥


እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤


የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል።


ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


አሌፍ። ወርቁ እንዴት ደበሰ! ጥሩው ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የመቅደሱ ድንጋዮች በጐዳና ሁሉ ራስ ተበተኑ።


ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ።


“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል’ ብሎ ተናገረ።


ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ምን እንዳደረግሁበት እዩ።


አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፤ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈራርሷል።


ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።


ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፥ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደ እዚያም ስፍራ ትሄዳላችሁ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ፈጽሜ እረሳችኋለሁ፥ እናንተንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ እጥላለሁ።


በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፤ ስለዚህ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ እሰጥሻለሁ።


“ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።


እንዲህም በላቸው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ለመሄድ እኔን ባትሰሙ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios