ኤርምያስ 45:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 አንተም ለራስህ ታላቅን ነገር ትሻለህን? አትሻ፥ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ነገር ግን በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልጋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልገው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ። Ver Capítulo |