ኤርምያስ 44:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ስለዚህም በግብጽ ምድር በዚያ ለመቀመጥ ከገቡት ከይሁዳ ትሩፍ ማናቸውም ተመልሰው ለመቀመጠጥ ወደ ሚመኙበት ወደ ይሁዳ ምድር አያመልጡም በሕይወትም አይተርፉም አይመለሱምም፤ ከአንዳንድ ከሚያመልጡ በቀር አይመለሱም።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ወደ ግብጽ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በይሁዳ ከስደት ተርፈው ወደ ግብጽ ወርደው ከሚኖሩት መካከል አንድ እንኳ የሚያመልጥ ወይም የሚተርፍ አይኖርም፤ እንደገና ይኖሩባት ዘንድ ወደሚናፍቋት ወደ ይሁዳ የሚመለስ ማንም አይኖርም፤ ከጥቂት ስደተኞች በቀር ተመልሶ የሚመጣ አይኖርም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በዚያ ለመቀመጥ በልባቸው ተስፋ ወደሚያደርጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሱ ዘንድ በግብፅ ለመኖር ከመጡ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፥ ወደዚያም የሚመለስ አይኖርም፤ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በዚያ ለመቀመጥ ወደ ግብጽ ምድር ከሄዱ፥ ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው በዚያ ይቀመጡ ዘንድ ከሚወድዱ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር ወደዚያም የሚመለስ የለም፥ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም። Ver Capítulo |