Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 34:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፥ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ አርነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችም እንዲሆኑላችሁ ገዛችኋቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አረከሳችሁ፤ ወደ ፈለጉበት እንዲሄዱ ነጻ የለቀቃችኋቸውንም ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎቻችሁን መለሳችሁ፤ እንደ ገናም ባሪያዎቻችሁ አደረጋችኋቸው።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነገር ግን እንደገና ሐሳባችሁን በመለወጥ ስሜን የሚያስነቅፍ ሥራ ሠራችሁ፤ ይኸውም ሁላችሁም እንደየፍላጎታቸው ነጻ የለቀቃችኋቸውን እንደገና ባሪያዎች አድርጋችሁ መግዛት ቀጠላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፥ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ አርነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን አስመለሳችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም እንዲሆኑላችሁ ገዛችኋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 34:16
15 Referencias Cruzadas  

በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።


ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።


ነገር ግን ከዚያ በኋላ ተመልሰው አርነት ያወጡአቸውን ወንዶችና ሴቶች ባርያዎቻቸውን አስመለሱ፥ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችም አድርገው ገዙአቸው።


“የጌታ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አያልፍም።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት።


“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።


ቅዱሱ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፥ ቅዱሱ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ እንዲሰደብ አልፈቅድም፤ አሕዛብም በእስራኤል ያለሁ ቅዱስ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።


ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios