Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 31:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲህም ይሆናል፤ እነርሱን ልነቅላቸውና ልሰባብራቸው፥ ላፈርሳቸውና ላጠፋቸው፥ ክፉም ላደርግባቸው እንደ ተጋሁ፥ እንዲሁ ልሠራቸውና ልተክላቸው እተጋለሁ፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ልነቅላቸውና ላፈርሳቸው፣ ልገለብጣቸውና ላጠፋቸው፣ መከራም ላመጣባቸው እንደ ተጋሁ ሁሉ፣ ላንጻቸውና ልተክላቸው ደግሞ እተጋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እነርሱን ለመንቀልና ለማፍረስ፥ ለመገለባበጥና ለማጥፋት፥ ለመደምሰስም እከታተል የነበርኩትን ያኽል፥ እነርሱን እንደገና ለመትከልና ለማነጽም እከታተላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ አፈ​ር​ሳ​ቸ​ውና ክፉ አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ እንደ ተጋ​ሁ​ባ​ቸው፥ እን​ዲሁ እሠ​ራ​ቸ​ውና እተ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እተ​ጋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲህም ይሆናል፥ አፈርሳቸውና ክፉ አድርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፥ እንዲሁ እሠራቸውና እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:28
24 Referencias Cruzadas  

“እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደነበረው ጊዜ፥ እንደ ፊተኛው ወራት ምነው በሆንሁ!


አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥


ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።


ሰማይና ምድር ባሕርም በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።


እነሆ፥ ዛሬ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፥ እንድታጠፋና እንድትገለባብጥ፥ እንድታንጽና እንድትተክል ሾሜሃለሁ።”


ጌታም “ቃሌን ልፈጽመው ነቅቼ እየጠበቅሁ ነኝና መልካም አይተሃል” አለኝ።


ዓይኔንም ለበጐነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።


ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል፥ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።


ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ ለእነርሱ የተናገርሁትን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።


ስላደረግሁባችሁ ክፉ ነገር ተጸጽቻለሁና በዚህች ምድር ብትቀመጡ አንጻችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፥ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።


እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እመለከታለሁ፤ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።


እንዲህ በለው፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሠራሁትን አፈርሳለሁ፥ የተከልሁትንም እነቅላለሁ፤ ይኸውም ምድሪቱን በሞላ ነው።


ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


የእስራኤልን ቤት ሰዎች ሁሉ ሙሉን በእናንተ ላይ አበዛለሁ፥ በከተሞቹም ሰዎች ይኖሩባቸዋል፥ የፈረሱት ስፍራዎችም ይሠራሉ፤


“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤


የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብኩ፥ እንዳልተጸጸትኩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥


እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን ለማድረግ አስቤአለሁ፤ አትፍሩ!


“‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደገናም እሠራዋለሁ፤


ጌታ በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደገና በአንተ ደስ ይለዋልና፥ ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ እንዲሁም በከብትህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ እጅግ ያበለጽግሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos