Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 25:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለእናንተ ጉዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ አስቆጣችሁኝ እንጂ አልሰማችሁኝም፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ነገር ግን አልሰማችሁኝም” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጃችሁ በሠራው ነገር አስቈጣችሁኝ፤ በራሳችሁም ላይ ክፉ ነገር አመጣችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን አልሰማችሁኝም፥ እጃችሁ በሠራው ጣዖት አስቆጣችሁኝ።’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለእ​ና​ንተ ጕዳት እን​ዲ​ሆን በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 25:7
15 Referencias Cruzadas  

በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቁጣዬን በማነሣሣታቸው ነው።”


እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”


ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ።


አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በምናምንቴዎቻቸውም አስቆጡኝ፥ እኔም በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፥ በማያስተውል ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ።


“ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሎቼን አልሰማችሁምና


እናንተም እንድትጠፉ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ እንድትሆኑ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት አጥናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?


ወደ ጌታም እንዲመልሱአቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፥ እነርሱ ግን አላደመጡም።


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”


በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፤ አንቺም፦ ‘አልሰማም’ አልሽ። ከሕፃንነትሽ ጀምሮ ድምፄን አለመስማትሽ መንገድሽ ነው።


ይህም የሆነው ቃሎቼን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል ጌታ፤ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ በተደጋጋሚ ላኩኝ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል ጌታ።’


አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ትሩፍ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ልጅንና ሕፃንን ከእናንተ ለማጥፋት ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios