Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 58:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁል​ጊዜ ከአ​ንተ ጋር ይኖ​ራል፤ እንደ ነፍ​ስ​ህም ፍላ​ጎት ያጠ​ግ​ብ​ሃል፤ አጥ​ን​ት​ህ​ንም ያለ​መ​ል​ማል፤ አን​ተም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ገነት፥ ውኃ​ውም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ምንጭ ትሆ​ና​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም ሁል ጊዜ ይመራሃል፥ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፥ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 58:11
35 Referencias Cruzadas  

እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።


ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።


አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።


ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥ ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።


የገነት ምንጭ፥ የሕይወት ውኃ ጉድጓድ፥ ከሊባኖስም የሚፈስሱ ወንዞች።


በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።


ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም መታደስ።


“ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆነች፤ የወደሙት፥ ባድማ የሆኑት፥ የፈረሱት ከተሞች አጥር ተሰርቶላቸዋል፥ መኖሪያም ሆነዋል” ይላሉ።


በጌታ ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።


በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር።


በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሮቹን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም በመጣ ጊዜ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም ከማፍራት እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”


ስግብግብ ሰው ክርክርን ያነሣሣል፥ በጌታ የሚታመን ግን ይጠግባል።


በአንተ ምክር መራኸኝ፥ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


በክፉ ዘመንም አያፍሩም፥ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።


ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥ በራብም ጊዜ በሕይወት ይጠብቃቸው ዘንድ።


የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።


በራብ ጊዜ ከሞት፥ በሰልፍም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።


አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ይምራ፤


ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።


የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።


እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።


በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።”


እኔ ጌታ ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጎዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።


ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።


መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለእርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እሰጣለሁ።


ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የጌታም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።


“ነገር ግን አምላክህ ጌታ ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርክህ፥ በመካከልህ ድኻ አይኖርም።


እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥ የበልግም ዝናብ በረከትን ይሰጣልና።


በፈሳሾችም አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች በሣር መካከል ይበቅላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios