Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 52:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ፥ ጉበኞችሽ ጮኸዋል፤ ጌታ ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዐይን በዐይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነሆ፥ የሚ​ጠ​ብ​ቁሽ ሰዎች ድምፅ ከፍ ከፍ ይላ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽዮ​ንን ይቅር ባላት ጊዜ ዐይን በዐ​ይን ይተ​ያ​ያ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት በቃ​ላ​ቸው ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፥ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 52:8
34 Referencias Cruzadas  

ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ዘበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው።


እኔን ለዘለዓለም በመፍራት ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።


በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል።


በዚያን ጊዜም ሁሉም የጌታን ሥም እንዲጠሩና በአንድ ትከሻ እንዲያገለግሉት፥ ለሕዝቦች ንጹሕን አንደበት እመልስላቸዋለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ፥ የአፌን ቃል በሰማህ ጊዜ ታስጠነቅቅልኛለህ።


እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።


እኔም፦ ‘የመለከቱን ድምፅ አድምጡ’ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አናደምጥም’ አሉ።


በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።


የምሥራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወደለው ተራራ ውጪ፤ የምሥራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፥ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፦ እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ።


ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።


ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።


አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።


ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።


በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥


በዚያም ቀን ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።


በዚያም ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፤ ቅጥሯንና ምሽጓን ለደኅንነታችን አኑሮታል።


እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ እልልም ይላሉ፥ ስለ ጌታ ክብርም ከባሕር ይጣራሉ።


ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።


ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።


ሃያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር “አሜን! ሃሌ ሉያ!” እያሉ ሰገዱለት።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።


የጌታን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፥


ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።


የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios