ኢሳይያስ 44:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በልቡም ማንም አያስብም፦ “ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን?” ለማለት እንኳን እውቀትና ማስተዋል የለውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ማንም ቆም ብሎ አላሰበም፤ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ስለሌለው እንዲህ ማለት አልቻለም፤ “ግማሹን በእሳት አቃጥዬዋለሁ፤ በፍሙ እንጀራ ጋግሬበታለሁ፤ ሥጋ ጠብሼበት በልቻለሁ፤ ታዲያ፣ በቀረው እንዴት ጸያፍ ነገር እሠራለሁ? ለግንድስ መስገድ ይገባኛልን?” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “የዚህን እንጨት ግማሹን አነደድኩት፤ በፍሙም ዳቦ ጋገርኩበት፤ ሥጋም ጠብሼበት በላሁ፤ አሁን እንግዲህ ቀሪውን ቊራጭ እንጨት ለጣዖት ላውለውን? በአንድ ቊራጭ እንጨት ፊት ወድቄ ልስገድን?” ብሎ የሚያስብ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ማንም በልቡ አያስብም፥ “ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፤ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም ዕውቀትና ማስተዋል የለውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፥ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም። Ver Capítulo |