Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 43:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሠረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፥ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፤ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣ እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ የጦር ሠራዊትንና ጀግኖችን ወደ ጥፋታቸው መራቸው፤ እነርሱ ወደቁ፤ ዳግመኛም አይነሡም፤ እፍ ሲሉት እንደሚጠፋ ጧፍም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና ፈረ​ሱን ሠራ​ዊ​ቱ​ንና አር​በ​ኛ​ውን ያወ​ጣል፤ እነ​ርሱ ግን በአ​ን​ድ​ነት ተኝ​ተ​ዋል፤ አይ​ነ​ሡም፤ ቀር​ተ​ዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስ​ታ​ሪም ጠፍ​ተ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፥ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፥ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 43:17
16 Referencias Cruzadas  

ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።


የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹ ከፈረሰኞቹም ጋር ወደ ባሕር ገቡ፥ ጌታም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ሄዱ።


የፈርዖንን ሰረገሎችና ሠራዊቱን በባሕር ጣላቸው፤ የተመረጡት መኮንኖችም በቀይ ባሕር ሰጠሙ።


ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፤ ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።”


በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሠረገላውንና በላዩ የሚቀመጠውን እሰባብራለሁ፤


ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፥ መንጠቆ በመንጋጋህ አስገባሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችን፥ ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ሁሉም ሰይፍ የያዙ ጋሻና ራስ ቁርን ካደረጉ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፥


ፍርድን ወደ ድል እስኪያመጣ ድረስ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆን አይሰብርም፤ የሚጤስን የጧፍ ክር አያጠፋም።


ባራቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሠራዊቱን እስከ ሐሮሼት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos