Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 39:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እርሱም፦ “በቤትህ ያዩት ምንድነው?” አለው፤ ሕዝቅያስም፦ “በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኢሳይያስም “በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤት ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “በቤ​ትህ ያዩት ምን​ድን ነው?” አለው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤቴ፥ እን​ዲ​ሁም በቤተ መዛ​ግ​ብቴ ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እርሱም፦ በቤትህ ያዩት ምንድር ነው? አለው፥ ሕዝቅያስም፦ በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፥ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም አለው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 39:4
8 Referencias Cruzadas  

ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን የታመነና ጻድቅ ነው፥ ከዓመፃም ሁሉ ያነጻናል።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


ቀና ብለህ እያየኸው ይጠፋል፥ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።


በደሌንም በውስጤ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰው ሰውሬ እንደሆነ፥


ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”


ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ?” አለው። ሕዝቅያስም፦ “ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ” አለው።


ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፦ “የሠራዊትን ጌታ ቃል ስማ።


በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios