ኢሳይያስ 35:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በዚያን ጊዜ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ምንጭ ይፈልቃልና አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የድዳም ምላስ ይዘምራል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ዐንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፤ የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል፤ ውሃ ከበረሓ ይወጣል፤ ምንጮችም ከምድረ በዳ ይፈልቃሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አንካሶች እንደ ሚዳቋ ይዘላሉ፤ መናገር የማይችሉ ድዳዎች ይዘምራሉ፤ በበረሓ ውስጥ የጅረት ውሃ ይፈስሳል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፥ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና። Ver Capítulo |