Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በሕዝብህ መካከል ሽብር ይነሣል፤ ምሽጎችህም ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ሰልማን ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ እናትም ከልጆችዋ ጋር ተዳምጣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰልማን፣ ቤትአርብኤልን በጦርነት ጊዜ እንዳፈራረሰ፣ እናቶችንም ከልጆቻቸው ጋራ በምድር ላይ እንደ ፈጠፈጣቸው፣ ሽብር በሕዝብህ ላይ ይመጣል፤ ምሽጎችህም ሁሉ ይፈራርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሕዝባችሁ ላይ ከባድ ጦርነት ይመጣል፤ ምሽጎቻችሁ ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ ይህም ንጉሥ ሸልማን የቤትአርቤልን ከተማ በጦርነት እንዳፈራረሰና እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ ፈጥፍጦ እንደ ጨረሰበት ጊዜ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በሕዝብህም መካከል ሽብር ይነሣል፥ እናትም ከልጆችዋ ጋር በተፈጠፈጠች ጊዜ ሰልማን ቤትአርብኤልን በሰልፍ ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 10:14
21 Referencias Cruzadas  

ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።


የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።


የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር ጦርነት በገጠመው ጊዜ ተሸንፎ እጁን በመስጠት በየዓመቱ ይገብርለት ጀመረ።


ለመሆኑ ከሌሎች ሕዝቦች አማልክት አንዱ እንኳ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አገሩን ያዳነ ይገኛልን?


ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤ የሶርያም ትሩፍ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል፤ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”


ሰውንም ከሰው ጋር፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ አላትማቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፥ አላዝንም፥ አልምርም።”


ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ሆኖአል።


ቤቴል ሆይ! ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ እንዲሁ ይደረግባችኋል፤ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።


“እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያውም ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።


አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?”


ጌታ የሠራዊት አምላክ ምድርን ይዳስሳል እርሷም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ዳግመኛም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች።


አስማትን ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ጠንቋዮችም ለአንተ አይሆኑም፤


ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።


ምሽግሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፤ በሚወዛወዙ ጊዜ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።


በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፥ ገዢዎችም መሳቂያ ሆነውላቸዋል፤ በምሽጎቹ ሁሉ ይስቃሉ፥ አፈሩን ከምረው ይወስዱታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos