Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤” ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አላየንም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።” እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ተገዝቶለት አናይም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረግህለት።” ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ሲያደርግ፤ በሥልጣኑ ሥር ሳያደርግለት ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ነገር ግን አሁን እንዳለ ሁሉ ነገር በእርሱ ሥልጣን ሥር እንደ ሆነ ገና አላየንም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ር​ገህ አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት።” ሁሉን ለእ​ርሱ ባስ​ገ​ዛ​ለት ጊዜም የተ​ወ​ውና ያላ​ስ​ገ​ዛ​ለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እን​ዳ​ስ​ገ​ዛ​ለት አና​ይም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 2:8
19 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደሰጠው፥ ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣና ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ አውቆ፥


“ሁሉን ነገር ከእግሩ ሥር አስገዝቶለታል” ተብሏልና፤ ነገር ግን፥ ሁሉን ነገር አስገዛለት ሲል፥ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥር እንዲገዛ ያደረገውን እግዚአብሔርን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።


ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፥ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


ነገር ግን ከመላእክት፥ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” ከቶ ለማን ብሎአል?


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


ስለ እርሱ የምንናገርለት፥ የሚመጣውን ዓለም ያስገዛው ለመላእክት አይደለምና።


አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።


በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ግን፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን፥፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios