Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 45:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወንድሞቹን ሁሉ ሳማቸው፥ በእነርሱም ላይ አለቀሰ፥ ከዚያም በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር ተጫወቱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከርሱ ጋራ መጨዋወት ጀመሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዮሴፍ የቀሩትንም ወንድሞቹን አንድ ባንድ እየሳመ አለቀሰ፤ ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መነጋገር ጀመሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወንድሞቹን ሁሉ ሳማቸው በእነርሱም ላይ አለቀሰ ከዚያም በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር ተጫወቱ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 45:15
17 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፥ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።


ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።


ዔሳውም ሊገናኘው ሮጦ ተጠመጠመበት፥ አንገቱንም አቅፎ ሳመው፥ ተላቀሱም።


ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዐይናቸው እያየ አሰረው።


የወንድሙን የብንያምንም አንገት አቅፎ አለቀሰ፥ ብንያምም በአንገቱ ላይ አለቀሰ።


በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ፥” በሰሙትም ነገር ፈርዖንና አገልጋዮቹ ደስ ተሰኙበት።


ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ፥ የግብጽ ሰዎችም ሰሙ፥ በፈርዖን ቤትም ተሰማ።


ዮሴፍም ሠረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ፥ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ።


ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ሄዶ ነገረው። ከዚያም ንጉሡ አቤሴሎምን አስጠራው፤ እርሱም መጥቶ በንጉሡ ፊት በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።


እግዚአብሔርን ሳስታውስ እተክዛለሁ፥ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።


ጌታም አሮንን፦ “ሙሴን ለመገናኘት ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው፤ ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፥ ሳመውም።


ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።


ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤


ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደገና አለቀሱ፥ ዖርፋም አማቷን ሳመች፥ ሩት ግን አማቷ ጋር ተጣበቀች።


ጌታም በየባላችሁ ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው። ሳመቻቸውም፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ።


ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?


ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos