Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህም የዚያ ጉድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህ የተነሣ የዚያ ምንጭ ስም፣ “ብኤርላሃይሮኢ” ተብሎ ተጠራ፤ እስካሁንም በቃዴስና በባሬድ መካከል ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ ሰዎች በቃዴስና በባሬድ መካከል የሚገኘውን የውሃ ጒድጓድ “ብኤር ላሐይ ሮኢ” ብለው ይጠሩታል፤ ትርጒሙም “ሕያው የሆነውና የሚያየኝ አምላኬ ጒድጓድ” ማለት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ጕድ​ጓድ ስም “በፊቴ የተ​ገ​ለ​ጠ​ልኝ የእ​ርሱ ጕድ​ጓድ” ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም በቃ​ዴ​ስና በባ​ሬድ መካ​ከል ነው። አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህም የዚያ ጕድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፤ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 16:14
7 Referencias Cruzadas  

ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


ከአብርሃም ሞት በኋላም እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው፤ ይስሐቅም ብኤር-ላሃይ-ሮኢ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ።


ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ፥ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና።


ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፥ ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና።


ተመልሰውም ቃዴስ ወደተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፥ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴቦን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ።


አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፥ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።


እግዚአብሔርም ዓይንዋን ከፈተላት፥ የውኃ ጉድጓድንም አየች፥ ሄዳም አቁማዳውን በውኃ ሞላች፥ ብላቴናውንም አጠጣች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios