Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ እንደሆንኩ “እንደ እኔ ሁኑ” ብዬ እለምናችኋለሁ። እናንተ አንዳችም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወንድሞች ሆይ፤ እለምናችኋለሁ፤ እኔ እናንተን እንደ መሰልሁ፣ እናንተም እኔን ምሰሉ። እናንተ አንዳች አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ ስለ ሆንኩ እናንተም እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ፤ እናንተ ምንም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ሁኛ​ለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ አን​ዳች አል​በ​ደ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 4:12
13 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ማንም ያሳዘነ ቢኖር፥ እኔን ብቻ ሳይሆን ያሳዘነው፥ ባላጋንነው በተወሰነ መልኩ፥ ሁላችሁንም ነው።


ኢዮሣፍጥንም “በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ለመዝመት ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢዮሣፍጥም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው” አለው።


እንደ እኛ ሆናችሁ ወንዶቻችሁን ሁሉ ብትገርዙ በዚህ ብቻ እሺ እንላችኋለን፥


ለእኔ ግን፥ ዓለም ለእኔ እኔም ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት አይሁንብኝ።


ነገር ግን እነርሱ ከወንጌሉ እውነት ጋር በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ፥ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፦ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እንደ አይሁድ ሳይሆን እንደ አሕዛብ የምትኖር ከሆነ፥ አሕዛብ አይሁድ እንዲሆኑ ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”


ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን ይህን እላችኋለሁ፤ እናንተም ደግሞ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።


ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።


ወንድሞች ሆይ! የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን።


የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ! በግልጽ ነግረናችኋል፥ ልባችንንም ለእናንተ ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል።


ምናልባት ስለ እናንተ በከንቱ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።


ቀድሞ በሥጋ ድካም ወንጌልን እንደሰበክሁላችሁ ታውቃላችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios