ገላትያ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ለአባቶች ወግ ከመጠን በላይ ቅናት ስለ ነበረኝ፥ በአይሁዳዊነት ወገኖቼ ከነበሩት እኩዮቼ ብዙዎችን እበልጥ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በእኔ ዕድሜ ዘመን ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ይበልጥ በአይሁድ ሃይማኖት እልቅ ነበር፤ ስለ አባቶቼም ወግ እጅግ ቀናተኛ ነበርሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የአይሁድን እምነት በመጠበቅ በዘመኔ ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቼ ሁሉ እበልጥ ነበር፤ ስለ አባቶችም ወግ ከፍተኛ ቅናት ነበረኝ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ለአባቶች ሥርዐት እጅግ ቀናተኛ ነበርሁና በወገኖች ዘንድ ከጓደኞች ሁሉ በአይሁድ ዘንድ እጅግ ከበርሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር። Ver Capítulo |