Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሁንም ትሩፋን እንዲያስቀርልን፥ በተቀደሰውም ስፍራው ችንካርን እንዲሰጠን፥ አምላካችንም ዓይናችንን እንዲያበራ፥ በባርነትም ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስን እንዲሰጠን ለጥቂት ጊዜ ከጌታ ከአምላካችን ሞገስ ተሰጥቶናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም ቅሬታ ይተ​ዉ​ልን ዘንድ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍ​ራው ኀይ​ልን ይሰ​ጠን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም ዐይ​ና​ች​ንን ያበራ ዘንድ፥ በባ​ር​ነ​ትም ሳለን ጥቂት የሕ​ይ​ወት መታ​ደ​ስን ይሰ​ጠን ዘንድ ለጥ​ቂት ጊዜ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥቂት ዕረ​ፍ​ትን አገ​ኘን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሁንም ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፥ በተቀደሰውም ስፍራው ችንካርን ይሰጠን ዘንድ፥ አምላካችንም ዓይናችንን ያበራ ዘንድ፥ በባርነትም ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ሞገስ ተሰጥቶናል።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 9:8
36 Referencias Cruzadas  

የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”


ባርያዎች ነን፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፥ የአምላካችንን ቤት እንድንሠራና ፍርስራሾቹን እንድንጠግን መታደስን ሊሰጠን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ግንብ ሊሰጠን በፋርስ ነገሥታት ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኛ ላይ ዘረጋ።


ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።


ነገር ግን አንተ ቸርና መሐሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፥ አልተውካቸውምም።


ይህም ነፍሱን ከመቃብር ይመልስ ዘንድ፥ በሕያዋንም ብርሃን ያበራ ዘንድ ነው።


እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?


አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ


በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።


ጌታን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከምፈራውም ሁሉ አዳነኝ።


በውኑ ለዘለዓለም ትቈጣናለህን? ቁጣህንስ ለልጅ ልጅ ታስረዝማለህን?


ድኀና ግፈኛ ተገናኙ፥ ጌታ የሁለቱንም ዐይን ያበራል።


የጠቢባን ቃል እንደ በሬ መውጊያ ነው፥ የተሰበሰቡትም ከአንድ እረኛ የተሰጡት ቃላት እንደ ተቸነከሩ ችንካሮች ናቸው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፤ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።


በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ሁሉ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”


ነቢዩንም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “በዐይኖችህ እንደምታየን ከብዙ ጥቂት ተርፈናልና ልመናችን እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ ስለ እኛና ስለዚህ ትሩፍ ሁሉ ለጌታ ለአምላክህ ጸልይ፥


ስለዚህም በግብጽ ምድር በዚያ ለመቀመጥ ከገቡት ከይሁዳ ትሩፍ ማናቸውም ተመልሰው ለመቀመጠጥ ወደ ሚመኙበት ወደ ይሁዳ ምድር አያመልጡም በሕይወትም አይተርፉም አይመለሱምም፤ ከአንዳንድ ከሚያመልጡ በቀር አይመለሱም።”


ነገር ግን እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን የሚያወጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ ወደ እናንተ ይመጣሉ፥ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር፥ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ።


ከሁለት ቀን በኋላ ነፍስ ይዘራብናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት ያኖረናል።


ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።


በመካከልሽ ትሑትና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብን አስቀራለሁ፤ በጌታም ስም ይታመናሉ።


ከእነርሱም የማእዘን ድንጋይ፥ ከእርሱም የድንኳን ካስማ፥ ከእርሱም የጦር ቀስት፥ ከእርሱም ገዥም ይመጣል።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፥ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠልአቸውን ይሰጣሉ፤ ለዚህም ቀሪ ሕዝብ ይህን ነገር ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ በተረፈው ሕዝብ ዐይን ነገሩ ቢያስደንቅ፥ በውኑ ለእኔ ግን አስደናቂ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ።


ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፦ “የእስራኤል ልጆች ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም ትሩፋን ይድናሉ፤


ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ወደፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለትም ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአዲሲቱን ኢየሩሳሌምን ስም፥ እንዲሁም አዲሱን ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


ነገር ግን ዮናታን አባቱ ሕዝቡን በመሐላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። ስለዚህ በእጁ የያዘውን ዘንግ ጫፍ በማሩ ወለላ ውስጥ በማስገባት እጁን ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።


ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos