Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አዛዡ ሬሑምና ጸሐፊው ሺምሻይ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዳኞቹ፥ ባለሥልጣኖቹ፥ አስተዳዳሪዎቹ፥ ጸሐፍያን፥ የኤርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱሳንካውያን፥ ዴሐውያን፥ ዔላማውያን፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ደብዳቤው የተጻፈው፣ ከአገረ ገዥው ሬሁም፣ ከጸሓፊው ሲምሳይ በትሪፖሊስ፣ በፋርስ፣ በአርክ፣ በባቢሎን እንዲሁም በሱሳ ማለትም በኤላማውያን ላይ ዳኞችና ገዦች ከሆኑት ከተባባሪዎቻቸው፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከአገረገዢ ረሑምና ከአውራጃው ጸሐፊ ሺምሻይ፥ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ከሆኑት ዳኞችና ቀድሞ በዔላም ምድር በኤሬክ፥ በባቢሎንና በሱሳ ይኖሩ ከነበሩት ሌሎችም ባለ ሥልጣኖች ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ፥ የቀ​ሩ​ትም ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዲና​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ት​ካ​ዋ​ያን፥ ጠር​ፈ​ላ​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ው​ያን፥ አር​ካ​ው​ያን፥ ባቢ​ሎ​ና​ው​ያን፥ ሱስ​ና​ካ​ው​ያን፥ ዴሐ​ው​ያን፥ ኤላ​ማ​ው​ያን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አዛዡ ሬሁም እና ጸሐፊው ሲምሳይ፥ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዲናውያን፥ አፈርሳትካውያን፥ ጠርፈላውያን፥ አፈርሳውያን፥ አርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱስናካውያን፥ ዴሐውያን፥ ኤላማውያን፥

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 4:9
16 Referencias Cruzadas  

የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።


አዛዡ ሬሑምና ጸሐፊው ሺምሻይ ኢየሩሳሌምን የሚመለከት አንድ ደብዳቤ ለንጉሡ ለአርጤክስስ እንዲህ ብለው ጻፉ፤


በዚያው ዘመን በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው ወደ እነርሱ መጥተው እንዲህ አሏቸው፦ “ይህን ቤት ለመሥራት፥ ቅጥሩንም ለማደስ ማን አዘዛችሁ?”


የደብዳቤውንም ግልባጭ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው በወንዙ ማዶ የነበሩ ባለ ሥልጣናት ወደ ንጉሡ ዳርዮስ ላኩለት፤


“አሁንም በወንዝ ማዶ ያለውን አካባቢ ገዢ የሆንህ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይ በወንዝ ማዶም ያሉ ተባባሪዎቻቸው ባለ ሥልጣናት ከዚያ ራቁ፤


መጥተው ኢየሩሳሌምን ሊወጉና ሊሸብሩ ሁሉም በአንድነት አሴሩ።


አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ።


የዘምሪ ነገሥታትንም ሁሉ፥ የኤላም ነገሥታትንም ሁሉ፥ የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥


በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።


ኤላምም በዚያ አለች ብዛትዋም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።


የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በመስጴጦምያም በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos