Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎቹ ምክር ንብረቱ ሁሉ ይወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህም ሁሉ በሕዝቡ መሪዎች ምክርና ትእዛዝ የተወሰነ ነበር፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ወደዚህ ስብሰባ መምጣት ያልቻለ ማንም ሰው ቢኖር ንብረቱ ሁሉ እንደሚወረስና ከምርኮ ከተመቱት ሰዎች ጉባኤ እንደሚወገድ ተነገረው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:8
14 Referencias Cruzadas  

ምርኮኞቹ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ።


በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።


የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ትእዛዝ በማያደርግ በማንም ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ንብረት መወረስ ወይም ግዞት በፅኑ ይፈረድበት።”


ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።


እንዲህም ሆነ ሕጉን በሰሙ ጊዜ የተደባለቀውን ዘር ሁሉ ከእስራኤል ለዩ።


“ነገር ግን ሰው የእርሱ ከሆነው ነገር ሁሉ ለጌታ ለይቶ እርም ያደረገው፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፥ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።


እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።


ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።


ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና።


መልሰው “አንተ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ተወልድህ፤ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።


በውጭ ባሉት ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።


ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ የናስና የብረትም ዕቃ ለጌታ የተቀደሰ ይሁን፤ ወደ ጌታም ግምጃ ቤት ይግባ።”


በምጽጳ፥ በጌታ ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፥ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በጌታ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ።


ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos