ዕዝራ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሣ፥ ወደ ኤልያሺብ ልጅ ወደ ይሆሐናን ክፍል ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን አዝኖ ነበርና በዚያ ገብቶ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኝነታቸውን ከማጕደላቸው የተነሣ ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ቀጥሎም ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበረው ስፍራ በመነሣት የኤልያሺብ ልጅ ዮሐናን ወደሚኖርባቸው ክፍሎች ገባ፤ ምርኮኞቹ እምነት በማጓደል ስለ ፈጸሙትም በደል ሁሉ እያዘነ ሌሊቱን በዚያው አነጋ፤ እህልም ሆነ ውሃ አልቀመሰም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤሊያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኀጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኃጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። Ver Capítulo |