Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከካህናቱ ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፥ ከዮፃዳቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ፥ ማዕሤያ፥ ኤሊዔዜር፥ ያሪብና ግዳልያ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከካህናት ዘሮች መካከል ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ዘሮችና ከወንድሞቹ መካከል፤ መዕሤያ፣ አልዓዛር፣ ያሪብና ጎዶልያስ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮጼዴቅ ልጆች ከሆኑት ከኢያሱና ከወንድሞቹ ጐሣ የተገኙ፤ ማዕሤያ፥ ኤሊዔዘር፥ ያሪብና ገዳልያ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከካ​ህ​ና​ቱም ወገን ልጆች እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ ከኢ​ያሱ ልጆ​ችና ከወ​ን​ድ​ሞቹ ማዓ​ሥያ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኦሬም፥ ገዳ​ልያ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ፥ መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብ፥ ጎዶልያስ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:18
27 Referencias Cruzadas  

እስከ መጀመሪያው ወር፥ መጀመሪያው ቀን ድረስ እንግዶች ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።


ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዔላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፋር፥ ከቢግዋይ፥ ከሬሁምና፥ ከባዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው።


ካህናቱ ከኢያሱ ቤት የሆነው ይዳዕያ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።


የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሣ፥ ወንድሞቹ ካህናትና፥ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹም በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሊያቀርቡበት የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።


በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።


በዚያን ጊዜ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸው የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።


እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ አለቆቹ ወደ እኔ ቀርበው፦ “የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም እንደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብጻውያንና አሞራውያን ርኩሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር ሕዝቦች እራሳቸውን አልለዩም፤


አንዳንድ ሴቶች ልጆቻቸውን ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስት አድርገው ወስደዋል፥ ቅዱሱንም ዘር ከምድር ሕዝቦች ጋር ደባልቀዋል፤ በዚህ አለመታመን የአለቆቹና የባለሥልጣኖቹ እጅ ቀዳሚ ነበር።”


ኢያሱም ዮያቂምን ወለደ፥ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፥ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፥


ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።


ጸሐፊውም ዕዝራ ለዚህ ተብሎ በተሠራ የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቅያና ማዓሴያ በቀኙ በኩል፤ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።


ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።


ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳውም ማሰማርዎች ደርቀዋል፤ አካሄዳቸውም ክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም።


ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ ሌላው ቀርቶ በቤቴ ውስጥ እንኳ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል ጌታ።


በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።


መበለቲቱንና የተፈታችውን ለሚስትነት አይውሰዱ፤ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር የሆነችውን ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረችውን መበለት ይውሰዱ።


ካህኑ ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና አመንዝራይቱን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም በባልዋ የተፈታችውን አያግባ።


በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የጌታን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል ሰሙ፥ አምላካቸው ጌታ ልኮታልና፤ ሕዝቡም በጌታ ፊት ፈሩ።


አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል ጌታ፤ ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፤ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱ፥ ይላል ጌታ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ከዚያም እርሱ ታላቁን ካህን ኢያሱን በጌታ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም እርሱን ለመክሰስ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።


ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፤ በሊቀ ካህኑ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፤ እንዲህም በለው፦


እንዲሁም ሴቶች መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ሐሜተኞች ያልሆኑ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos