Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በጌታ መቅደስ መግቢያ፥ በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ነበሩ፥ ጀርባቸው ወደ ጌታ መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ሃያ ዐምስት ሰዎች ያህል ነበሩ፤ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አድርገው ለምትወጣዋ ፀሓይ ይሰግዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ በውስጥ በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ወሰደኝ፤ እዚያም ወደ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ኻያ አምስት ያኽል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ጀርባቸውን ወደ መቅደሱ አድርገው የምትወጣዋን ፀሐይ በማምለክ ወደ ምሥራቅ ተንበርክከው ይሰግዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 8:16
29 Referencias Cruzadas  

‘ስሜ ይጠራበታል’ ወዳልከው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ፤ አገልጋይህም በዚህ ስፍራ የምጸልየውን ጸሎት ስማ።


ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤


በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፤


የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፤ ለዚሁ አምልኮ የሚያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፤ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለ ሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጽር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፤


በይሁዳ ከተማዎችና በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ባሉት ስፍራዎች ሁሉ በየኰረብታው ላይ በነበሩት መሠዊያዎች መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ የይሁዳ ነገሥታት ሾመዋቸው የነበሩትን ካህናት ሁሉ ከሥራ አሰናበተ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ፥ ለፀሐይ፥ ለጨረቃ፥ ፀሐይን ለሚዞሩ ዓለማትና ለከዋክብት መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉ ካህናትን ሁሉ ሻረ፤


አባቶቻችን ተላልፈዋል፥ በአምላካችንም በጌታ ፊት ክፉ አድርገዋል፤ እርሱንም ትተዋል፥ ፊታቸውንም ከጌታ መኖሪያ መልሰዋል፥ ወደ እርሷም ጀርባቸውን አዙረዋል፤


ሰሎሞንም በጌታ ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን ውስጥ ቀደሰ፤ ሰሎሞን የሠራው የናስ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ስቡንም መያዝ አልቻለምና የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት ስብ በዚያ አቀረበ።


ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ድንጋዩንም፦ ‘አንቺ ወለድሺኝ’ ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ‘ተነሥተህ አድነን’ ይላሉ።


ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ባለማቋረጥ ባስተምራቸውም እንኳ ተግሣጽን ለመቀበል አልሰሙም።


ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ እንዳደረግነው፥ ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።


እኔን ለማስቆጣት፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ፥ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ፤ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቁርባን ያፈስሳሉ።


በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።


ሰውዬው ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ በደቡብ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላው።


መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው ወደ ጌታ ቤት ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ። እነሆም በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን መሪዎች የዓዙርን ልጅ ያአዛንያንንና የበናያ ልጅ ፈላጥያንን አየሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለረሳሽኝ፥ ወደ ኋላሽም ስለጣልሽኝ፥ አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ።


ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ፥ በዚያው ቀን ሊያረክሱት ወደ መቅደሴ ገብተዋልና፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ ይህን አደረጉ።


በደቡብ በር በኩል ወዳለው ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ የደቡብንም በር ለካ፤ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበረው።


ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር።


መንፈስም አነሣኝ፥ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አስገባኝ፤ እነሆ፥ የጌታ ክብር ቤቱን ሞላው።


መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውን በመቃኔ አጠገብ በማድረጋቸው፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ቀረ፥ በሠሩት ርኩሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፥ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።


ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ የቤቱን መቃኖችና የመሠዊያው ጠርዝ በአራቱ ማዕዘን፥ የውስጠኛውም አደባባይ የበሩን መቃኖች ይቀባ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።


ምድር በደም ፍርድ ተሞልታለች፥ ከተማም በዓመፅ ተሞልታለችና፥ ሰንሰለት ሥራ።


እርሱም፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኩሰት ታያለህ” አለኝ።


የጌታም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ “አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤” ከአሕዛብ መካከል፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ስለምን ይበሉ?


ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፥ ለእርሱም ማለትም ለፀሓይ ወይም ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፥


ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ፥ ጌታ አምላካችሁ ከሰማይ በታች ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸውን፥ ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም፥ የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ፥ በመሳት እንዳትሰግዱላቸውና እንዳታመልኳቸው ተጠንቀቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos