ሕዝቅኤል 48:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ከይሁዳ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምታቀርቡት መባ የሚሆን ድርሻ ይሆናል፤ ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል፥ ከድርሻዎቹ እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከይሁዳ ነገድ ድንበር ጋር የተያያዘ ቦታ ለይታችሁ ትመደባላችሁ፤ ይህም ቦታ ወርዱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ከሌሎች ነገዶች ድርሻ ጋር ከምሥራቅ ጐን እስከ ምዕራብ ጐን ድረስ እኩል ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም የሚገኘው በዚህ ቦታ መካከል ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 “ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የተለየ ክፍል ይሆናል፤ ወርዱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የሆነ የዕጣ ክፍል ይሆናል፥ ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል። Ver Capítulo |