ሕዝቅኤል 47:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በሰሜኑ በር በኩል አወጣኝ፤ በውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በውጭ ወዳለው በር አመጣኝ፤ እነሆ ውኃው በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ከዚያም በሰሜኑ በር በማውጣት በውጭ አዙሮ በምሥራቅ አቅጣጫ ወዳለው የውጭ በር መራኝ፤ ውሃውም በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ያም ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል ከቤተ መቅደሱ አውጥቶ ወሰደኝ፤ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ በሚመለከተውም ቅጽር በር አዞረኝ፤ ከቅጽር በሩም በስተ ደቡብ ውሃው ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፤ በስተ ውጭ በአለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፤ እነሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈስስ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፥ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፥ እነሆም፥ ውኃው በቀኙ ወገን ይፈስስ ነበር። Ver Capítulo |