Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 47:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ረግረጉና እቋሪው ውኃ ግን አይፈወስም፤ ጨው እንደሆነ ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነገር ግን ረግረጉና ዕቋሪው ውሃ ንጹሕ አይሆንም፤ ጨው እንደ ሆነ ይቀራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ነገር ግን ረግረጉና እቋሪው ውሃ የጨው መከማቻ እንደ ሆነ ይቀራል እንጂ የጠራ ውሃ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ረግ​ረ​ጉና ዕቋ​ሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖ​ራል እንጂ አይ​ፈ​ወ​ስም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እረግረጉና እቋሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይፈወስም።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 47:11
11 Referencias Cruzadas  

ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፤ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ፤” አለ።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


እርሱ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ ነው፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይቀመጥበት፥ ጨው ባለበት ምድር፥ በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።


ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።


በዚያን ዕለት አቤሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማይቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማይቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት።


በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉ አይረግፍም ፍሬውም አያልቅም፤ ውኃው ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኩር ያፈራል፤ ፍሬው ለመብል ቅጠሉም ለፈውስ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios