ሕዝቅኤል 43:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የመሠዊያውም ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም አንድ ክንድ ከስንዝር ነው። መሠረቱ ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፥ ዙሪያውም አንድ ስንዝር ጠርዝ አለው፤ ይህም የመሠዊያው ከፍታ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “የመሠዊያው ልክ በረዥም ክንድ ይህ ነው፤ ይኸውም ክንድ ከስንዝር ማለት ነው፤ ቦዩ አንድ ክንድ ጥልቀት፣ አንድ ክንድ ወርድ ያለው ሲሆን፣ ዙሪያው አንድ ስንዝር ጠርዝ አለው፤ የመሠዊያውም ከፍታ ይህ ነው፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የመሠዊያውም ልክ እንደሚከተለው ነው፦ መሠዊያው ያረፈበት አንድ ረጅም ክንድ ርዝመትና አንድ ረጅም ክንድ ወርድ ሲሆን የዙሪያ ጠርዙም ስፋት አንድ ስንዝር ነው፤ ይህም ረጅም ክንድ በሌላው አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል፤ ይህም የመሠዊያው ከፍታ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የመሠዊያው ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም ክንድ ተጋት ነው። የመሠረቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስንዝርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙሪያው አለ፤ የመሠዊያው ቁመት እንዲሁ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የመሠዊያውም ልክ በክንድ ይህ ነው ክንዱም ክንድ ተጋት ነው። የመሠረቱም ቁመቱ አንድ ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፥ አንድ ስንዝርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙሪያው አለ፥ የመሠዊያው መሠረት እንዲሁ ነው። Ver Capítulo |