ሕዝቅኤል 42:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በሦስት ደርብ ተሠርተው ነበርና፥ በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ፥ አዕማድ አልነበሩአቸውም፥ ስለዚህ ላይኞቹ ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እነርሱም በሦስት ፎቆች የተሠሩ ሲሆኑ እንደ ውጪው አደባባይ ሕንጻዎች ዐምዶች አልነበሩአቸውም። ስለዚህ የላይኛው ፎቅ ክፍሎች ከሁለተኛው ፎቅና ከምድር ቤቱ ክፍሎች ይልቅ ወደ ውስጥ ገባ ያሉ ነበሩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በሦስትም ደርብ ተሠርተው ነበርና፥ በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ፥ አዕማድ አልነበሩላቸውምና ስለዚህ ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በሦስትም ደርብ ተሠርተው ነበርና፥ በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ፥ አዕማድ አልነበሩላቸውምና ስለዚህ ላይኞቹ ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ። Ver Capítulo |