Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 42:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በፊታቸው የነበረው መንገድም በሰሜን በኩል ያሉትን ክፍሎች ይመስል ነበር። ርዝመታቸውም፥ ወርዳቸውም፥ መውጫቸውም አቀማመጣቸውና መግቢያዎቻቸውም ተመሳሳይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋራ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በክፍሎቹም ፊት ለፊት መተላለፊያ ነበር፤ ክፍሎቹ ልክ በሰሜን በኩል እንዳሉት ክፍሎች ርዝመትና ወርዳቸው፥ መውጫዎቻቸውና የበሮቻቸው አቀማመጥ ተመሳሳይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በስ​ተ​ፊ​ታ​ቸ​ውም የነ​በረ መን​ገድ በሰ​ሜን በኩል እንደ ነበ​ረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መን​ገድ አም​ሳል ነበር። ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም፥ መው​ጫ​ቸ​ውም፥ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ውም፥ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በዚ​ያው ልክ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በሰሜን በኩል እንደ ነበረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መንገድ ምስያ ነበረ። ርዝመታቸውም ወርዳቸውም መውጫቸውም ሥርዓታቸውም መዝጊያዎቻቸውም በዚያው ልክ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 42:11
4 Referencias Cruzadas  

ከክፍሎቹም ፊት ለፊት በውስጥ በኩል ወርዱ ዐሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መንገድ ነበረ፤ መግቢያዎቹም በሰሜን በኩል ነበሩ።


በሠሩት ሥራ ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ፥ የቤቱን ንድፉንና አሠራሩን፥ መውጫውንና መግቢያውን፥ አጠቃላይ ንድፉን፥ ሥርዓቱን ሁሉ፥ ንድፉን ሁሉ፥ ሕጉን ሁሉ አሳውቃቸው፤ ንድፉን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ እንዲያዩትና እንዲያደርጉትም በፊታቸው ጻፈው።


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።


የከተማይቱ መውጫዎች እነዚህ ናቸው። በሰሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos