ሕዝቅኤል 40:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)48 ወደ ቤቱም መተላለፊያ አገባኝ፥ የመተላለፊያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም48 ወደ ቤተ መቅደሱም መተላለፊያ በረንዳ አመጣኝ፤ የመተላለፊያ በረንዳዎቹን ዐምዶች ለካ፤ በአንዱ በኩል ዐምስት ክንድ በሌላውም እንዲሁ ዐምስት ክንድ ነበር። የመግቢያው በር ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ ሲሆን፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ስፋት በአንዱ በኩል ሦስት ክንድ፣ በሌላውም እንዲሁ ሦስት ክንድ ነበሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም48 ከዚያ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ ክፍል አመጣኝ፤ የመግቢያው ክፍል የግድግዳውም ዐምዶች ሲለካ የሁለቱም ትይዩ አምስት ክንድ ሆኖ አገኘው፤ የመግቢያውም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበር፤ የመግቢያውም ግድግዳ ውፍረት በሁለቱም በኩል ሦስት ሦስት ክንድ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)48 ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመጣኝ፤ የደጀ ሰላሙንም የግንብ አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ፤ በዚያም ወገን አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)48 ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመጣኝ፥ የደጀ ሰላሙንም የግንብ አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፥ የበሩም ወርድ አሥራ አራት ክንድ ነበረ፥ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ። Ver Capítulo |