Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የኃጢአቱን መሥዋዕትና የበደሉን መሥዋዕት እንዲያርዱባቸው፥ በበሩ መተላለፊያ በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 በመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳው ሥር በግራና በቀኝ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት የሚታረዱበት ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 በመግቢያው ክፍል በኩል በግራና በቀኝ ትይዩ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ በእነዚያም ጠረጴዛዎች ላይ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትና ለበደል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ይታረድባቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዱ​ባ​ቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የኃጢአቱንና የበደሉንም መሥዋዕት ያርዱባቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:39
22 Referencias Cruzadas  

መስፍኑ ከውጭ በኩል ባለው በር በመተላለፊያ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


በመንግሥቴም ከእኔ ማዕድ ትበላላአችሁ፥ እንዲሁም ትጠጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይም ለመፍረድ በዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ።


እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት።


“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።


ወደ መቅደሴም ይገባሉ እኔን ለማገልገል ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴን ይጠብቃሉ።


እንዲህም አለኝ፦ በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ ጌታ የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቁርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።


ከእንጨት የተሠራው መሠዊያ ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ነበር፥ ማዕዘኖቹ፥ እግሩና ግድግዳው ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ እርሱም፦ “ይህ በጌታ ፊት ያለ ገበታ ነው” አለኝ።


ለሚቃጠለው መሥዋዕት ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል፥ ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመታቸው ደግሞ አንድ ክንድ የሆኑ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕት የሚያርዱበትን ዕቃዎች የሚያስቀምጡባቸው፥ ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ገበታዎች ነበሩ።


ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።


እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።


ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።


ከመተላለፊያው በስተ ውጭ በሰሜን በኩል ባለው በር መግቢያ አጠገብ፥ ሁለት ገበታዎች ነበሩ፥ በበሩ መተላለፊያ በሌላኛው ወገን በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ።


በበሩ አጠገብ በዚህ ወገን አራት ገበታዎች በዚያም ወገን አራት ገበታዎች ነበሩ፤ መሥዋዕት የሚያርዱባቸው ገበታዎች ስምንት ነበሩ።


“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።


እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው፤ በእውነት በጌታ ፊት በደለኛ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios