ሕዝቅኤል 39:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ወጥተው፥ የጦር መሣሪያዎችን፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 “ ‘ከዚያም በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ወጥተው የጦር መሣሪያውን፣ ትልልቁንና ትንንሹን ጋሻ፣ ቀስቱን፣ ፍላጻውን፣ የጦር ዱላውንና ጦሩን ሰብስበው ማገዶ በማድረግ ያነድዱታል፤ ሰባት ዓመት ይማግዱታል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ወጥተው የተጣለውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ለእሳት ማገዶ እንዲሆን ይሰበስባሉ፤ ጋሻውን፥ ቀስቱን፥ ፍላጻውን፥ ጦሩንና ዱላውን ሁሉ ሰብስበው ያነዱታል፤ ለሰባት ዓመት የሚበቃም ማገዶ ይኖራቸዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፤ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ አላባሽ አግሬ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፥ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ ጎመድንና ጦርንም ያቃጥላሉ፥ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። Ver Capítulo |