Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 37:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የጌታን ቃል ሰሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለእነዚህ ዐጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘እናንተ ደረቅ ዐጥንቶች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እርሱም እንዲህ አለ፦ “ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ብለህ ትንቢት ተናገር፦ እናንተ ደረቅ አጥንቶች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “በእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ እና​ንተ የደ​ረ​ቃ​ችሁ አጥ​ን​ቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 37:4
17 Referencias Cruzadas  

ነቢዩም ጌታ ባዘዘው መሠረት ያንን መሠዊያ በመቃወም እንዲህ ሲል የትንቢት ቃል ተናገረበት፦ “መሠዊያ! መሠዊያ ሆይ! ጌታ ስለ አንተ የሚለው ቃል ይህ ነው፦ ‘እነሆ ለዳዊት ቤተሰብ ኢዮስያስ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ይወለዳል፤ እርሱም በኮረብታ ላይ ለተሠራው ለአሕዛብ መሠዊያ አገልጋዮች ሆነው መሥዋዕት የሚያቀርቡብህን ካህናት በአንተው ላይ ያርዳቸዋል፤ የሰዎችንም አጥንት በአንተ ላይ ያቃጥላል።


ቁርበትና ሥጋ አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አጠንከርኸኝ።


ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።


እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።


ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የጌታን ቃል ስሚ።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሙ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።


ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ መቃብራችሁን እከፍታለሁ፥ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ።


እንዲህም አለኝ፦ “ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር የሰው ልጅ ሆይ፥ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ በሕይወት እንዲኖሩ በእነዚህ በተገደሉት ላይ እፍ በልባቸው።’”


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ የጌታን ወቀሳ ስሙ፤ ጌታ ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይዋቀሳልና።


“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።”


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤


እናቱም ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፤” አለቻቸው።


“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።


“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos