Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 37:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲህም አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን?” እኔም “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ዐጥንቶች በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ብቻ ታውቃለህ” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች ዳግመኛ ሕይወት የሚያገኙ ይመስልሃልን?” አለኝ። እኔም “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህን የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ” አልኩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አንተ ታው​ቃ​ለህ” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 37:3
14 Referencias Cruzadas  

አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


“የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው።


እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንደሚችል አስቦአልና፤ ይስሐቅን እንደ ምሳሌ መልሶ ተቀበለ።


እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ እንደሆነ ስለምን በእናንተ ዘንድ የማይታመን ነገር ሆኖ ይቆጠራል?


ጌታ ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ከሲኦልም ያወጣል።


አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር!


ነገር ግን አንዱ፥ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚወጡትስ በምን ዓይነት አካል ነው?” ብሎ ቢጠይቅ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ጥልቁንም በላይሽ ላይ ባመጣሁብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆችም ይከድኑሻል፥


በእነርሱ ላይ በዙሪያቸው አሳለፈኝ፤ እነሆ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፤ እነሆም፥ በጣም የደረቁ ነበሩ።


በውኑ ለሙታን ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህን? ጥላዎችስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios