ሕዝቅኤል 36:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 “ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር አለኝ፦ የባዕድ አገር ሕዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ምድራችሁን ስላፈራረሱትና በእርግጥም ባድማ ስላደረጉት አገራችሁ ለሌሎች ሕዝቦች ንብረት ሆነ። እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችኋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና Ver Capítulo |