ሕዝቅኤል 31:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አልሸፈኑትም፥ ጥዶችም ቅርጫፎቹን አይመስሉትም አስታ የሚባለውም ዛፍ ቅርጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ በእግዚአብሔር ገነት የነበረ ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያሉ ዝግባዎች፣ ሊወዳደሩት አልቻሉም፤ የጥድ ዛፎች፣ የርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤ የኤርሞን ዛፎችም፣ ከርሱ ቅርንጫፎች ጋራ አይወዳደሩም፤ በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ በውበት አይደርስበትም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ያለው የሊባኖስ ዛፍ ሊወዳደረው አይችልም፤ የጥድ ዛፍም ቅርንጫፉን አያኽልም፤ የግራር ዛፎች ቅርንጫፍ ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር ሲወዳደር እንደ ኢምንት ነው። በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸው እንኳ እንደ እርሱ ያለ ውበት የላቸውም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አይተካከሉትም፥ ጥዶችም ቅርንጫፎቹን፥ አስታ የሚባለውም ዛፍ ጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ገነት ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አላጨለሙትም፥ ጥዶችም ቅርጫፎቹን አስታ የሚባለውም ዛፍ ጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፥ የእግዚአብሔርም ገነት ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመሳሰለውም ነበር። Ver Capítulo |