ሕዝቅኤል 29:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፥ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋር አጣብቃለሁ፤ በቅርፊትህ ከተጣበቁት የወንዞችህ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህ መካከል አወጣሃለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ነገር ግን በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋራ አጣብቃለሁ፤ ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት ዓሦች ሁሉ ጋራ፣ ከወንዞችህ ጐትቼ አወጣሃለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በመንጋጋህ መቃጥን አስገባለሁ፤ በወንዝህ ውስጥ ያሉትንም ዓሣዎች በሰውነትህ ላይ እንዲጣበቁ አደርጋለሁ፤ ዓሣዎቹም በአንተ ላይ እንደ ተጣበቁ ከዓባይ ወንዝ ጐትቼ አወጣሃለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በመንጋጋዎችህ መቃጥን አገባብሃለሁ፤ የወንዞችህንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ፤ ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ፤ የወንዞችህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ ይጣበቃሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በመንጋጋህ መቃጥን አገባብሃለሁ፥ የወንዞችህንም ዓሦች ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ፥ ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ፥ የወንዞችህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ ይጣበቃሉ። Ver Capítulo |