Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ፤ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጠባቂ ኪሩብ ሆነህ ተቀብተህ ነበር፤ ለዚሁም ሾምሁህ፤ በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንተን እንደ ጠባቂ ኪሩብ አድርጌ በመሾም በዚያ መደብኩህ፤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ትኖር ነበር፤ እጅግ በሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ትመላለስ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አንተ ልት​ጋ​ርድ የተ​ቀ​ባህ ኪሩብ ነበ​ርህ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ላይ አኖ​ር​ሁህ፤ በእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተመ​ላ​ለ​ስህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ፥ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፥ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 28:14
22 Referencias Cruzadas  

የመገናኛውን ድንኳንና የምስክሩን ታቦት በእርሱ ትቀባለህ፥


የቅባቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን እና በእርሱ ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፥ እርሱን፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅዱስም ይሆናል።


ነገር ግን እንድትቆም ያደረግኩት ኃይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ ላይ እንዲታወጅ ነው።


መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።


ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።


አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።


የጌታ ክብር ከቤቱ መግቢያ ወጥቶ ከኪሩቤል በላይ ቆመ።


በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው በምድሩ ላይ ያመልኩኛል፤ በዚያም እቀበላቸዋለሁ፥ በዚያም ቁርባናችሁን በኩራታችሁንም የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እፈልጋለሁ።


በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ድንጋይ ሁሉ ልብስህ ነበር፥ ያቁት፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፤ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፤


እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።


“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይላሉ።


ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos