ሕዝቅኤል 26:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ዘውዳቸውን ከራሳቸው ያወርዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ፤ በመሬትም ላይ ተቀምጠው ይደነግጣሉ፤ ሞታቸውንም ይፈራሉ፤ ስለ አንቺም ያለቅሳሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፥ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፥ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ በአንቺም ይደነቃሉ። Ver Capítulo |